መከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Other Sale
- Posted Date : 06/12/2022
- Phone Number : 0114352148
- Source : Reporter
- Closing Date : 06/28/2022
Description
መከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት
DEFENCE CONSTRUCTION MATERIALS MANUFACTURING ENTERPRISE
የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ ቁጥር 04/2014
መከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. ያገለገሉ የእንጨት ምርት ውጤቶች (የተለያዩ መጠን ያላቸው የእንጨት በርና መስኮቶች ከPVC የተሰሩ በሮች፣ መስኮቶች … ወዘተ)
ሎት 2. ያገለገሉ የሳኒተሪ ዕቃዎች (የሽንት ቤት መቀመጫ፣ የፊት መታጠቢያ ሳህን፣ የውሃ ማሞቂያ (ቦይለር)፣ የፊት መታጠቢያ ሳህን መስታወት…ወዘተ
ስለዚህ በዘርፋ የተሰማሩ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው& የአቅራቢነት& የአምራችነት ወይም አስመጪ የምስክር ወረቀት እና የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ አምራቾች፣ አቅራቢዎች እና አስመጪዎች በጨረታው እንዲሳተፋ እየጋበዘን ዝርዝር የጨረታ መመሪያ እና ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀኖች ቃሊቲ በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤታችን ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል እና ሰነዱን በመግዛት መጫረት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታዉ ማክሰኞ ሰኔ 21/2014 በ4፡00 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳወቃለን፡:
ማሳሰቢያ፡–
የማሳያ ግዜ ከሰኔ 13/2014 እስከ ሰኔ 17/2014 ዘወትር በሥራ ሰዓት
ጠዋት ከ3፡00 —– ሰዓት 5፡30
ከሰዓት ከ8፡00 —- 10፡00 ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡:
አድራሻ፡– ቃሊቲ ከቶታል አልፎ ቋራ ሆቴል አጠገብ ይገኛል፡፡
ማስታወሻ፡– ለተጨማሪ ማብራሪያ የስልክ ቁጥር 0114-35-21-48/49/50/ ወይም
0114- 34-87 43/45 መደወል ይቻላል፡፡