የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የ2013 በጀት አመት ሒሳብ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Premier-league-s.c-logo

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 06/12/2022
 • Phone Number : 0911641427
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/17/2022

Description

 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ

የጨረታ ማስታወቂያ

   የጨረታ ቁጥር EPL/010/06/22

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የ2013 በጀት አመት ሒሳብ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲቲንግ ቦርድ (AABE) ስም ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሱ የኦዲት፣ ድርጅቶች የሚከተሉትን ተያያዥ መረጃዎች በማዘጋጀት እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

 1. የድርጅቱ የኦዲት ቡድን ብቃትና ተሞክሮ ማቅረብ፡፡
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ፡፡
 3. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
 4. የሌሎች ድርጅቶችን ኦዲት በተሳካ ሁኔታ መስራቱን የሚያሳይ ማስረጃና የሥራ ልምድ ማቅረብ፡፡
 5. የኦዲት ሥራውን የሚያጠናቅቅበትን ጊዜ ማሳወቅ የሚችል፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ5(አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በድርጅቱ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ጨረታው ዓርብ ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 9፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-

ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር በሚያስኬደው መንገድ ከወንጌላዊት ሕንጻ 50 ሜትር

ከፍ ብሎ፣ የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤ/ክርስቲያን ህንጻ ፊት-ለፊት፣ ሜይስዊ ህንፃ ላይ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502፣

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911641427 / 0916023688 መደወል ይችላሉ፡