አፍሪካን ኔትወርክ ፎር ዘ ፕሪቬንሽን ኤንድ ፕሮቴክሽን አጌንስት ቻይልድ አቢዩዝ ኤንድ ኔግሌክት (አንፕካን) የድርጅቱ ንብረት የሆነ አንድ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡

ANPPCAN-Ethiopia-logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 06/12/2022
 • Phone Number : 0115505202
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/27/2022

Description

በድጋሚ የወጣ የመኪና ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

 አፍሪካን ኔትወርክ ፎር ዘ ፕሪቬንሽን ኤንድ ፕሮቴክሽን አጌንስት ቻይልድ አቢዩዝ ኤንድ ኔግሌክት (አንፕካን) – ኢትዮጵያ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በፈቃድ ቁጥር 0385 የተመዘገበ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነዉ፡፡ አንፕካን ኢትዮጵያ የድርጅቱ ንብረት የሆነ አንድ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ማንኛውም ተጫራች ጨረታዉ በሚካሄድበት ቀን መኪናዉ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት በጨረታው ተወዳድሮ  መግዛት ይችላል፡፡

የመኪናዉ አጠቃላይ መረጃ፤

 • ቶዮታ ላንድ ክሩዘር ሞዴል HZJ80L የታርጋ ቀጥሩ ኮድ 35-1117 የሆነ ያገለገለ መኪና የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 700,000.00 ባለበት ሁኔታ ለማሸጥ ይፈልጋል፡፡
 • የመኪናዉን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች መኪናዉ ባለበት የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ጉርድ ሾላ ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ህንፃ እና ከበሻሌ ሆቴል መካከል ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ ያለበት ህንፃ ግቢ ውስጥ በመገኘት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማለትም ከሰኔ 7  ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ3፡00 – 5፡00 ከሰዓት ከ8፡00 – 10፡00 ሰዓት ማየት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች ለሚጫረቱበት መኪና ያስገቡበትን ዋጋ 20% (ሀያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) አሰርቶ በጨረታው ቀን ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
 • ጨረታው ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት መኪኖቹ በሚገኙበት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል፡፡
 • በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሰኔ 7 ቀን 2014  እስከ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ  የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከአንፕካን-ኢትዮጵያ ዋና መ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት  ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት ዋናዉንና ኮፒዉን በተለያዩ ፖስታ በማደረግና ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ላይ በሌላ ፖስታ ዉስጥ አድረግዉ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 • ድርጅቱ የጨረታዉን አሸናፊ በደብዳቤ የሚያሳዉቅ ሲሆን ዉጤቱን ለተሳታፊዎች በግልጽ በማስታወቂያ ቦርድ በመለጠፍ የሚያሳዉቅ ይሆናል፡፡
 • የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉንና መኪናዉን እንዲረከብ በደብዳቤ ድርጅቱ ካሳወቀበት ማግስት ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት ውስጥ ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ መኪናውን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ተሰርዞ ለሐራጅ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ በጨረታው ተሳትፈው ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
 • የጨረታው አሸናፊ ለስም ማዛወሪያና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎችን በሙሉ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ለተጨማሪ በስልክ ቁጥር 0115505202/01115502222 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አንፕካን ኢትዮጵያ