የቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለኮሌጁ የተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

St.-Lideta-College-Health-Science-logo

Overview

 • Category : Office Items & Equipment Supplies
 • Posted Date : 06/12/2022
 • Phone Number : 0115157987
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/24/2022

Description

  ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለኮሌጁ የተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት-1 ልዩ ልዩ ቋሚ የቢሮና መማሪያ ክፍል ፈርኒቸር እቃዎች

ሎት-2 ቋሚ የፅህፈት መሳሪያዎች

ሎት-3 ቋሚ የህንፃ መሳሪዎች(ጀነሬተር፣ ግራይንደር)

ሎት-4 የማስታወቂያ ቦርድ ስራ

ሎት-5 የዌብ ሳይት ዲዛይን ስራ(website design & development service)

ሎት-6 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች

ሎት-7 ለቢሮ ፓርቲሽን ስራ የሚያገለግሉ ብረት እና MDF ጣውላዎች

በዚሁ መሰረት፡

 1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 10% ከባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው ብዛትና ስፔሲፊኬሽን መሰረት መሆን አለበት፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር (አምስት መቶ ብር) በኮሌጁ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሂሳብ ቁጥር 1000217747221 በማስገባት ያስገቡበትን የባንክ ደረሰኝ በመያዝ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ በስራ ሰዓት ከ2፡00 እስከ 11፡00 ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ እስከ 6፡00 ድረስ በቅድስት ልደታ የጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ በሚገኘው የኮሌጁ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 መግዛት ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
 6. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ሆኖ የሚከፈተው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይሆናል፡፡
 7. የጨረታው አሸናፊ 10% ባሸነፉበት እቃ መጠን የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
 8. የዕቃው ርክክብ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ የሚፈፀም ሲሆን የትራንስፖርት ወጭ በአቅራቢው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
 9. አቅራቢዎች ለሚያቀርቡት ዕቃ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ቀድመው ናሙናማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡በአካል ማቅረብ የማይቻል ክብደት ላላቸው እቃዎች ሲሆኑ በግልፅ በሚታይ ፎቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- ቅድስት ልደታ ቤተ-ክርሰትያን አጠገብ የሚገኘው ልደታ ህንፃ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0115157987 / 0115508338