ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የሚሆን የግብርና ግብዓቶችን ማለትም የእርሻ መሳሪያ፣ የፍራፍሬ ችግኝ፣ የጓሮ አትክልት ዘር እንዲሁም የእንሰሳት መኖ ሳር ግንጣዮችን/ቁርጥራጮችን ህጋዊነት ካላቸውና በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Flora & Horticulture
- Posted Date : 06/12/2022
- Phone Number : 0116477233
- Source : Reporter
- Closing Date : 06/24/2022
Description
የግብርና ግብዓቶች ግዢ ጨረታ
ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ እ ኤ አ ከ 2006 ጀምሮ በኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና፣እንሰሳት አያያዝ፣ተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ፣የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ቅነሳ እና መሰል የልማት ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡
በአሁን ሰዓት ድርጅቱ ከስታር ባክስ ፋውንዴሽን /Starbucks Foundation/ ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል በንሳ ወረዳ የሚገኙ ቡና አብቃይ ሴት አርሶ አደሮችን አቅም ማጎልበት /”Empowering Women in Coffee Growing Communities in Bensa District”/ ለተባለው ፕሮጀክት ተጠቃሚ አርሶ አደሮች የሚሆን የግብርና ግብዓቶችን ማለትም የእርሻ መሳሪያ፣ የፍራፍሬ ችግኝ፣ የጓሮ አትክልት ዘር እንዲሁም የእንሰሳት መኖ ሳር ግንጣዮችን/ቁርጥራጮችን ህጋዊነት ካላቸውና በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁ ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዶቻችሁን ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ አድርሻ በማስገባት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ መደብ /Lot / 1፦ የግብርና መገልገያ ቁሳቁሶች
ተቁ | የእቃው ዓይነት | መለኪያ | ብዛት | ምርመራ | ||
1. | አካፋ | በቁጥር | 90 | ባለ ዶሮ (ኦርጅናል) | ||
2. | ዛቢያ | በቁጥር | 135 | ባለ ዶሮ (ኦርጅናል) | ||
3. | ሬክ /መቧጠጫ | በቁጥር | 45 | ጣቱ ወፍራም የሆነ (አንደኛ ደረጃ) ባለ12 ጣት | ||
4. | የውሃ ማጠጫ | በቁጥር | 270 | ናትራን ባለ 10 ሊትር | ||
5. | ማጭድ | በቁጥር | 90 | አልቪን ኦሪጂናል | ||
6. | ሾድራ /ገሶ | በቁጥር | 45 | ባለ አዞ ኦሪጅናል/ | ||
7. | መኮትኮቻ | በቁጥር | 270 | ባለ 2 ጥርስእጀታው ሙሉ ብረት የሆነ ጠንካራ | ||
8. | ዶማ | በቁጥር | 270 | ባለ እንድ ጥርስ 2ኪሎ ክብደት | ||
የጨረታ መደብ / Lot / 2፦ የፍራፍሬ ችግኝ
ተ.ቁ | የዕቃው ዝርዝር | መለኪያ | ብዛት | ምርመራ |
1 | አቮካዶ ችግኝ | ችግኝ | 4050 | – ዝርያ፡ ሃስ፣ ችግኞቹ በፓሊቲን ቲዩብ የለማ፣
– ለተከላ በቂ የእድገት ደረጃ ላይ የደረሰ፣ – ችግኞቹ የተተከሉበት ፖሊቲን ቲዩብ ስፋት ቢያንስ 20 ሴ ሜ ስፋትና ከ20 እስከ 30 ሴ ሜ ቁመት – ችግኞቹ ጤናማና የማንኛውም ተባይና በሽታ የጸዱ መሆን አለባቸው
|
2 | አፕል ችግኝ | ችግኝ | 2700 | – ዝርያ፡ አና፣ፕሪንሲሳ፣ክሪስፒን፣ያታካ፣ ጆናጎ ሬድ፣ የተዳቀለ፣ ከበሽታ ነጻ፣ለተከላ በቂ እድገት ላይ ያለ |
3 | የቡና ችግኝ | ኝግኝ | 2700 | – ዝርያ 74110 እና 74112 በፖሊቲን ቲዩብ የለማ፣ የቱብ ስፋት 16ሴሜትር፣ ከበሽታ ነጻ |
የጨረታ መደብ /Lot/ 3፡ የጓሮ አትክልት ዘር
ተቁ | የእቃው አይነት | መለኪያ | ብዛት | ምርመራ |
1. | ካሮት/carrot | ኪሎ ግራም | 25 | – Nantus/ ናንተስ |
2. | ቀይስር /beetroot | ኪሎ ግራም | 25 | – Detroit dark red ዴትሪዮት ዳርክ ሬድ |
3. | ጥቅል ጎመን/head cabbage | ኪሎ ግራም | 25 | – Copenhagen /ኮፐንሃገን |
4. | ቆስጣ / Swiss chard | ኪሎ ግራም | 25 | – Ford hook giant/ፎርድ ሆክ ጂያንት |
5. | ቅይ ሽንኩርት/Onion | ኪሎ ግራም | 25 | – ቦምቤ ሬድ/ Bombe Red |
6. | ቲማቲም ዘር/Tomato seed | ኪሎ ግራም | 45 | ገሊላማ፣ ሮማ ቪ ኤፍ፣ መልካ ሳልሳ |
የጨረታ መደብ /Lot/ 4፡ የእንሰሳት መኖ ሳር ግንጣይና ዘር
ተቁ | የእቃው አይነት | መለኪያ | ብዛት | ምርመራ |
1. | የዝሆኔ ሳር /Elephant/Napier grass | ቁርጥራጭ | 80,000 | – ከበሽታ ነጻ፣ቢያንስ ሶስት እንቡጦች ያሉት |
2. | የደሾ ሳር /Desho Grass | ግንጣይ | 80,000 | – ከበሽታ ነጻ የሆነ |
3. | አልፋልፋ ዘር/Alfalafa | ኪግ | 70 | – የጥራት መጠኑ ከ95 በመቶ በላይ፣ የብቅለት መጠኑ ከ85 በመቶ በላይ የሆነ |
4. | የእንሰሳት ጓያ ዘር/Vetch seed | ኪግ | 100 | – የጥራት መጠኑ ከ95 በመቶ በላይ፣ የብቅለት መጠኑ ከ85 በመቶ በላይ የሆነ |
5. | ሲናር ዘር/Oat seed | ኪግ | 300 | – የጥራት መጠኑ ከ95 በመቶ በላይ፣ የብቅለት መጠኑ ከ85 በመቶ በላይ የሆነ |
6. | ዴዝሞዲየም ዘር//Desmodium seed | ኪግ | 20 | – ባለ አረንጓዴ ቅጠል፣የጥራት መጠኑ ከ95 በመቶ በላይ፣ የብቅለት መጠኑ ከ85 በመቶ በላይ የሆነ |
- ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነትና ለ2014 ዓም የተደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ተጫራቾች መወዳደር ለሚፈልጉት የጨረታ መደብ በተለያየ ፖስታ በማሸግና የጨረታ መደቡን ቁጥር በመጻፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአካል ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ መደብ 2 እና 4 ለተጠቀሱት የእቃ አይነቶች ተጫራቾች የራሳቸው የሆነ የግብርና ግብዓት ማምረቻ ማሳ እንዲሁም ከሚመለከተው የመንግስት አካል የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸው የገባል፡፡
- እያንዳንዱ ተጨራች የዋጋውን 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጥ ሰንድ /CPO/ ማስያዝ የጠበቅበታል፡፡
- አንድ ድርጅት በአንዱ ወይም በሁሉም የጨረታ መደቦች መሳተፍ ይችላል፡፡
- የጨረታ ማስገቢያ ፖስታው ላይ የጨረታው መደብና ቁጥር መገለጽ ይኖርበታል፡፡
- ተጨራቾች በተጠየቁ ጊዜ ዋጋ ያስገቡለትን ቁሳቁስ ናሙና ለማሳየት ወይም ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻችሁን ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ ማስገባት ይኖርባችኋል፡
- የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ አድራሻ፡
ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ሲ ኤም ሲ መንገድ፣ ከጊብሰን ት/ቤት ፊት ለፊት ጎልጎታ ህንጻ 7ተኛ ፎቅ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
ስልክ (+251)-11-6-47-72-33/34 +251 9 11 70 41 65
ወይም
ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ሲዳማ ክልል በንሳ ፕሮጀችት ጽ/ቤት ዳዬ ከተማ
ስልክ፡ +251 973 50 66 81