ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ለደንበኞቹ የካሳ ክፍያ ፈፀሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሸከርካሪዎች፣ ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ አካል ቅሪቶችንና ፋክስ ማሽኖች፣ ስካነር አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

The-United-Insurance-Company-Logo-Reportertenders

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 06/12/2022
 • Phone Number : 0111263434
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/29/2022

Description

ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ለደንበኞቹ የካሳ ክፍያ ፈፀሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሸከርካሪዎች፣ ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ አካል ቅሪቶችንና በባህር ጉዞ ጉዳት የደረሰባቸው ልዩ ልዩ ዕቃዎችን፣ ያገለገሉ የሻወር ትሪ እና ገንዳ፣ ያገለገሉ የቢሮ ጠረጴዛዎች፣ ተሽከርካሪ ወንበሮች፣ የእንግዳ ወንበሮች፣ የእንጨት ሼልፎች፣ ፋክስ ማሽኖች፣ ስካነር አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን የተሽከርካሪዎችንና የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘውን ፎርም ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት እንዲሁም ቃሊቲ በሚገኘው ሪከቨሪ ከሰኔ 06 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ሰነዱን በመውሰድ ዲ.ኤች.ገዳ ብርድልብስ ፋብሪካ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ እስከ ሰኔ 21 ቀን 2014 . ድረስ በሥራ ሰዓት በመምጣት ማየት ይቻላል፡፡
 2. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ወይም ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ እስከ ሰኔ 21 ቀን 2014 . ከቀኑ 10:30 ሰዓት ድረስ በኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ለተሽከርካሪዎቹም ሆነ ለዕቃዎቹ በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሠረት ለሕብረት ኢንሹራንስ አማ /The United Insurance Company SC/ ተብሎ በሲፒኦ የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉ ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡ አሸናፊዎች በጨረታው ላሸነፉት ንብረት ቀሪውን ክፍያ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ከሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
 4. የጨረታ አሸናፊዎች የተሽከርካሪዎችንም ሆነ የዕቃዎችን ሙሉ ክፍያ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምረው ከከፈሉ በኋላ ተሽከርካሪዎችንና ዕቃዎችን በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያሸነፉትን ንብረት ከፍለው ካልወሰዱ ኩባንያው አሸናፊውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ከመሆኑም በላይ ዕቃዎቹን ጨረታ በማውጣትም ሆነ ያለጨረታ የመሸጥ፣ የተሸጠበትን ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው:: በተጨማሪም ተጫራቾቹ ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም፡፡
 5. ተሽከርካሪዎች በጨረታ እስከ ተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር ጨረታውን አሸንፈው የሚገዙት አይጠየቁበትም፡፡ ተሽከርካሪዎቹ ከተሸጡ በኋላ በመንግስት የሚፈለግ የክፍያ ጥያቄ ቢኖር የመክፈል ኃላፊነቱ የገዥው ይሆናል፡፡
 6. ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችን ኩባንያው ለገዢዎች የሚያስረክበው ገዢዎች በቅድሚያ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሚወስነውን የቀረጥና ታክስ ክፍያ ከፍለው ተገቢውን ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ይሆናል፡፡
 7. ገዥዎች ተሽከርካሪዎችን ከገዙና ከተረከቡ በኋላ ከክልሎች የሚመጡ ፋይሎችና ክሊራንሶች ቢኖሩ ተከታትለው የሚያመጡት እነርሱ ይሆናሉ፡፡
 8. ተጫራቾች ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ከተረከቡ በኋላ በ6ወር ጊዜ ውስጥ የስም ዝውውር ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ከ6ወር በኋላ ከስም ዝውውር ጋር በተያያዘ ለሚቀርቡ ጥያቄዎችና ችግሮች ኩባንያው ሃላፊነት አይወስድም፡፡
 9. ጨረታው ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን 2014 . ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111- 26 34 34 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡