ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለጹትን የከባድ ተሸከርካሪ ጎማዎች ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው የሀገር ውስጥ አምራቾችና አቅራቢዎች ላይ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Tyre & Battery
- Posted Date : 06/13/2022
- Phone Number : 0114163273
- Source : Reporter
- Closing Date : 06/21/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ
Purchase bid No.02/Heavy Truck Tyre/2022
ኩባንያችን ከዚህ በታች የተገለጹትን የከባድ ተሸከርካሪ ጎማዎች ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው የሀገር ውስጥ አምራቾችና አቅራቢዎች ላይ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Lot | TYRE WITH INNER
TUBE SIZE |
UoM | NEEDED
QTY. |
REMARK |
Lot 1 | 14R25 | Pcs | 50 | OFF-ROAD DUMP TRUCK |
Lot 2 | 12R20 | Pcs | 100 | Foton and Sino Truck |
ማንኛውም ተጫራች ስለጨረታው እና የጎማውን ዝርዝር እና ተያያዥ መመሪያዎችን የያዘውን የጨረታ ሠነድ ከድርጅታችን ዋናው መስሪያ ቤት ካዛንቺስ ኢሊሌ ሆቴል አዲሱ ህንፃ ከሚገኘው ህንጻ 19ኛ ፎቅ ሶርሲንግ እና ግዢ መምሪያ በመቅረብ በሚሰጡት የኢሜይል አድራሻ ሰነዱን በመውስድ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ፡- ብር 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር ብቻ) : በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በድርጅቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን የደረሰኙን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራች ድርጅቶች የምታቀርቡትን የጎማ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መሰረት በማቅረብ ሆለታ ፋብሪካችን ድረስ የምታቀርቡበትን የነጠላ ዋጋ እና ተያያዥ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ እስከ ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ከላይ በተመለከተው የድርጅታችን ዋና መ/ቤት አድራሻ እንድታስገቡ እንጠይቃለን፡-
ጨረታው ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ከላይ በተገለጸው አድራሻ በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ
ስልክ ቁጥር 011-4163273