በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልግሎት የማይጋፋ የልማት ሀሳብ ያላቸው የቤተክርስቲያኗ አባል የሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማልማት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Tewahido-Church-logo-Reportertenders

Overview

  • Category : House & Building Rent
  • Posted Date : 06/13/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/30/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት

በአቃቂ ቃ//ከተማ ወረዳ 06 ክልል ውስጥ የሚገኘው

የሳሪስ ም/ቅዱሳን ፈ/ሕይወት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ገዳም ሰ/ /ቤት

በገዳሙ የይዞታ ማረጋገጫ በካርታ ቁጥር 015868 በተረጋገጠው ይዞታ ግቢ ውስጥ በስተደቡብ አቅጣጫ ከሳሪስ አቦ አደባባይ 80 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝና 30 ሜትር መንገድ የሚያዋሰነው ስፋቱ 640 ካ.ሜትር የሆነ ደረጃ አንድ ቦታ ለባንክ፣ ለኢንሹራንስ፣ ለመጋዘን፣ ለቢሮ፣ ለት/ቤት ወዘተ. የቤተክርስቲያኗን አገልግሎት የማይጋፋ የልማት ሀሳብ ያላቸው የቤተክርስቲያኗ አባል የሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማልማት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ባለሀብቶች፡-

  1. ቦታው ላይ ይዞት ለሚቀርበው የልማት ሀሳብ በራሱ ወጪ አስገንብቶና ተከራይቶ ለመሥራት የተስማማና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አማኝ እንዲሁም በሰበካ ጉባኤ አባልነት ተመዝግቦ መንፈሳዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ፣
  2. የልማት ሀሳብ ይዞ የሚቀርበው አልሚ/ባለሀብት በቦታው ላይ ለሚያከናውናው የልማት ሀሳብ ዝርዝር ጥናት ወይም የሥራ ሀሳብ እና በቦታው ላይ ልማቱ ቋሚ ወይም ጊዜአዊ (ማለትም ለምን ያህል ጊዜ ወይም ዓመት እንደሚቆይ) ጠቅሶ ማቅረብ የሚችል፣
  3. ተጫራቹ ባለሀብት በቦታው ላይ ለሚካሄደው የሕንፃ ግንባታም ሆነ ሌላ የልማት ስራ አገልግሎት በቂ ካፒታል እንዳለው የሚያሳይ የባንክ ስቴትመንት በጨረታ ውድድሩ ላይ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
  4. የልማት ሀሳብ ይዞ የሚቀርበው አልሚ/ባለሀብት ወይም ቦታውን የሚከራየው ባለሀብት በየወሩ ለቤተክርስቲያን የሚከፍለውን የኪራይ መጠን በካሬ ሂሳብ መግለጽ የሚችል፣
  5. አጠቃላይ ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ ሰነድ የተዘጋጀ መሆኑን እያሳሰብን ከላይ የተገለጸውን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ሁሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰኔ 5 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ ጨረታውም ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 3፡30 ሰዓት ሲሆን የገዳሙ ሰበካ ጉባዔ አባላትና የሚመለከታቸው ተወካዮች እንዲሁም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት የጨረታ ሰነዱ ተከፍቶ አሸናፊው የሚታወቅበት እና በዝርዝር አፈፃፀም ወደ ሥራ የሚገባ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- የገዳሙ ሰበካ ጉባኤ በወጣው የጨረታ ማስታወቂያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ    ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተቀመጠ ነው፡፡