ካናዳ ሀኪሞች የልማትና እርዳታ ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ መኪናዎች እና ሞተር ሣይክሎች የመንግስት ግብር የከፈሉ በዚሁ ስራ የተሠማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል፡፡

Canadian-Physician-for-Aid-and-Relief-CPAR-logo

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 06/15/2022
  • Phone Number : 0116295197
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/30/2022

Description

ያገለገሉ መኪኖች እና ሞተሮች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ 

 የጨረታ ቁጥር  002

ድርጅታችን የካናዳ ሀኪሞች የልማትና እርዳታ ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በቀን 15/09/2011 መሰረት የውጭ ሀገር በጒ አድራጐት ድርጅት ሆኖ በኤጀንሲው መመዝገቡ እና በመዝገብ ቁጥር 0888 ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት አግኝቶ በአገሪቱ ህግና ደንብ መሰረት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ድጋፍ እየሰጠ ያለ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡

የካናዳ ሀኪሞች የልማትና እርዳታ ድርጅት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ  ድርጅቶች ኤጀንሲ በቀን ጥር 06/2012 ዓ.ም  በደብዳቤ ቁጥር 10/ACSO/9934 በተፃፈ ደብዳቤ  ባገኘው ፈቃድ መሠረት ድርጅቱ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ መኪናዎች እና ሞተር ሣይክሎች የስም ዝውውር የማይጠየቅባቸው  ባሉበት ሁኔታ ሕጋዊ አሮጌ መኪና መግዛት ለሚችሉና  የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ለሚችሉ ማንኛውንም የመንግስት ግብር የከፈሉ በዚሁ ስራ የተሠማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ   15  ቀናት ማለትም  ከሐሙስ ሰኔ 09 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐሙስ  ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ  4፡00  ሠዓት  ገርጂ  ሮባ ዳቦ ጀርባ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር  ላይ በሚገኘው መስሪያቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የማይመለስ 150.00 ብር (አንድ መቶ ሀምሣ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ዋጋ ማቅረቢያቸውን እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃዳቸውን በሰም የታሽገ ኤንቨሎፕ አድርገው  በድርጅቱ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10% ሲፒዮ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐሙስ  ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ ሕጋዊ መታወቂያ ወይም ሕጋዊ ውክልና እና የጨረታ ሰንድ ግዥ የተፈጸመበትን ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታው አሸናፊዎት የጨረታ አሸናፊነታቸው ውጤት ከተገለፀ በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አስፈላጊውን ክፍያ ፈፅመው ንረታቸውን ከድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም 

አድራሻ  የካናዳ ሀኪሞች የልማትና እርዳታ ድርጅት ገርጂ ሮባ ዳቦ ጀርባ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር ላይ ስልክ ቁጥር  0116295197