አዋሽ ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀድሞ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት የተሻሻለው የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 1159/2011 አክሲዮኖች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Awash-Bank-logo-Reportertenders-4

Overview

 • Category : Share Foreclosure
 • Posted Date : 06/19/2022
 • Phone Number : 0115570092
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/24/2022

Description

የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 አዋሽ ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀድሞ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት የተሻሻለው የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 1159/2011 ከመውጣቱ በፊት የውጭ ዜግነት ከያዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን አክሲዮኖች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ጨረታ (ሎት) ለጨረታ የቀረቡ አክሲዮኖች ሰርተፍኬት ቁጥር የአክሲዮኖቹ ብዛት የአንዱ አክሲዮን መነሻ ዋጋ የአክሲዮኖቹ ጠቅላላ መነሻ ዋጋ
1 2234፣ 04236፣ 05729፣06535፣09997፣ 12437፣ 15051፣16720፣ 20123 ፣23873 ፣29426፣ 30348፣ 0036184፣ እና 44600 863 1,000.00 863,000.00  
2 08432፣10797፣13201፣17532፣21160፣2297926938 እና 33275 251 1,000.00 251,000.00  
3 13223፣ 15557፣ 17602፣ 19137፣ 22539፣ 25191፣31554 እና 06633 179 1,000.00 179,000.00  
4 27985፣31620፣0039879 እና 44599 88 1,000.00 88,000.00  
5 02419 እና 16937 5 1,000.00 5,000.00  
 

በመሆኑም፡

 1. የኢትዮጵያ ዜጋ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን መመሪያ የሚያሟሉ የውጭ ዜጎች እና ድርጅቶች በጨረታው በመሳተፍ መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አክሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ከጨረታው ቀን በፊት ከባንኩ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ባለአክሲዮኖች አገልግሎት ዋና ክፍል ብር 100 (አንድ መቶ) ከፍለው በመውሰድ ቅጹን ሞልተው በኤንቨሎኘ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ባለአክሲዮኖች አገልግሎት ዋና ክፍል ማስገባት አለባቸው፡፡
 3. ጨረታው ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ባለአክሲዮኖች አገልግሎት ዋና ክፍል ይከፈታል፡፡
 4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን አክሲዮኖቹን የሚጫረቱበትን ዋጋ 1/4 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ቅጹ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች በቀረበ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
 6. አንድ ላይ በቀረቡ ሰርተፍኬት ቁጥሮች (ሎት) የቀረቡ አክሲዮኖችን ከፋፍሎ ዋጋ ማቅረብ/መጫረት፤ በተጨማሪም በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 7. ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆናቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች ከሆኑ ቢጫ (የሎ) ካርድ እና ፓስፖርት ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 8. ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጎች የሆኑ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው በውጭ ምንዛሪ ሲሆን ጨረታውን ካሸነፉም ክፍያ መፈፀም የሚቻለው ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሪ ብቻ ነው፡፡
 9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
 10. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአምስት /5/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
 11. ተለያይተው የቀረቡትን አክሲዮኖች መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ለእያንዳንዱ ጨረታ (ሎት) በተለያየ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 12. በሌሎች ሕጎችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ሕጎች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡
 13. ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አዋሽ ባንክ

ለተጨማሪ መረጃ 0115-57-00-92/0115571823

አዋሽ ባንክ ፖ.ሣ.ቁ 12638 አዲስ አበባ