ተስፋ ድርጅት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ለመጭው የትምህርት ዘመን ለ2015 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተማሪዎች ደንብ ልብስ ጨርቅ፣ ጫማ እና የትምህርት መሳሪያዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 06/19/2022
- Phone Number : 0118723619
- Source : Reporter
- Closing Date : 07/04/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ተስፋ ድርጅት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ደቡብ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉን ቅርንጫፎች በትምህርት ፣ በሙያ ስልጠና እና በዕለት እርዳታ ዙሪያ የሰብአዊ አገልግሎት ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡ ድርጅታችን ለመጭው የትምህርት ዘመን ለ2015 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተማሪዎች ደንብ ልብስ ጨርቅ፣ ጫማ እና የትምህርት መሳሪያዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ | የዕቃው አይነት | መለኪያ | ብዛት | አይነት | ምርመራ |
አልባሳት | |||||
1 | የአገር ውስጥ ቴትሮን 6000 1ኛ ደረጃ (የተለያየ ቀለም) | ሜትር | 8973
|
በሚሰጠው ናሙና መሰረት | |
2 | ቦብሊን ወፍራም (የተለያየ ቀለም) | ሜትር | 556 | በሚሰጠው ናሙና መሰረት | |
3 | ቆዳ ጫማ የወንድ (ቁጥር ከ24 – 36) | ጥንድ | 799 | ጠንካራ ሶል ያለው | |
4 | ቆዳ ጫማ የሴት (ቁጥር ከ24 – 36) | ጥንድ | 892 | ጠንካራ ሶል ያለው | |
5 | ቆዳ ጫማ የወንድ (ቁጥር ከ37 – 45) | ጥንድ | 997 | ጠንካራ ሶል ያለው | |
6 | ቆዳ ጫማ የሴት (ቁጥር ከ37 – 45) | ጥንድ | 839 | ጠንካራ ሶል ያለው | |
7 | ሰንደል ጫማ የወንድ (ቁጥር ከ28 – 45) | ጥንድ | 193 | ጠንካራ ሶል ያለው | |
8. | ሰንደል ጫማ የሴት (ቁጥር ከ28 – 45) | ጥንድ | 206 | ጠንካራ ሶል ያለው | |
9 | ሸራ ጫማ የወንድ (ቁጥር 37-45) | ጥንድ | 278 | ጠንካራ ሶል ያለው | |
10 | ሸራ ጫማ የሴት (ቁጥር 37-45) | ጥንድ | 297 | ጠንካራ ሶል ያለው | |
የጽህፈት መሣሪያዎች | |||||
9. | ደብተር
– 32 ሉክ ባለመስመር – 50 ሉክ ባለመስመር – 100 ሉክ ባለመስመር – 50 ሉክ እስኪየር ደብተር – 32 ሉክ የስዕል ደብተር |
በቁጥር በቁጥር በቁጥር በቁጥር በቁጥር |
15,290 45,124 8,770 3,774 4,224 |
ነጭ ወረቀት፣ባለ መስመር፤ጠንካራ ሽፋን ያለው፤ቀለም የማያስተላልፍ |
|
10. |
ሰማያዊ እስክርቢቶ |
በቁጥር
|
46,256
|
የማይቆራረጥ፤በቀላሉ የማይሰበር፤ ቀለም የማይተፋ |
|
11 | ላፒስ | በቁጥር | 7,828 | ሲያጠፋ የማያጠቁር ፤በቀላሉ የማይፈረፈር፤ጠንካራ | |
12 | እርሳስ (HD) | በቁጥር | 11,314 | HB;ጠንካራ፤ደማቅ ጥቁር፤እንጨቱ ሲቀረጽ የማይፈረፈር ከላይ ላዺስ ያለው | |
13 | መቅረጫ | በቁጥር | 6,308 | በደንብ የሚቀርጽ፤ በቀላሉ የማይሰበር | |
14 | ማስመሪያ | በቁጥር | 5,433 | ኘላስቲክ የማይለመጥ |
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ስለ ጨረታው አፈፃጸም የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ እና ናሙና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር100 (አንድ መቶ ብር) አየር ጤና ከሚገኘው ዋናው ቢሮ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመግዛት ሞልተው ሊያስገቡ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ተጫራÓች ባስያዙት ናሙና መሰረት ዕቃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፣ ከቀረበው ናሙና ውጪ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የሚያስገቡአቸውን ሰነዶች በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡
- የአስተሻሸጐን ሁኔታ በተመለከተ ፋይናንሽሉን በአንድ ፓስታ ቴክኒካሉን ደግሞ በሌላ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻም ሁለቱንም በአንድ ፖስታ መታሸግ አለበት፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች የሚያቀርበውን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፐኦ /CPO/ ብቻ በድርጅቱ ስም አሰርቶ እስከ ሰኔ 24/2014 ዓ/ም ከቀኑ 10.00 ሰአት ድረስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡ ከሚያቀርበው ጥቅል ዋጋ 5% በታች /CPO/ የሚያቀርብ ለውድድሩ ብቁ አይሆንም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት፡- የልብሱ ጨረታ ሰኔ 27 /2014 ከጠዋቱ 3.00 ሰዓት፣ የጫማው ሰኔ 28 /2014 ከጠዋቱ 3.00 ሰዓት ሲሆን፣ የጽህፈት መሣሪያው ሰኔ 29 /2014ዓ.ም ከጠዋቱ 3.00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- የቀረቡትን ዝርዝሮች በትክክል አሟልቶ ያልፈፀመ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
አድራሻ፡-
ተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት
አየር ጤና፡- ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት
የመ.ሳጥን ቁጥር 30153
ስልክ ቁጥር- 0118723619/0113482537
አዲስ አበባ