የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቦከስ ፋይሉን እና ወረቀቱን በመለየት ለሚገዛ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው የወረቀት ፋብሪካዎች /አምራቾች/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Disposal Sale
- Posted Date : 06/19/2022
- Phone Number : 0114167347
- Source : Reporter
- Closing Date : 07/01/2022
Description
የ ጨ ረ ታ ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
ኮርፖሬሽናችን አዲስ አበባ-ጎተራ አካባቢ በሚገኘው ግቢ ውስጥ 10 ኮንቴነሮች ውስጥ የሚገኙ ሰነዶች እና ቦክስ ፋይሎች ባሉበት ሁኔታ በጥቅል ወይም ቦከስ ፋይሉን እና ወረቀቱን በመለየት ለሚገዛ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው የወረቀት ፋብሪካዎች /አምራቾች/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሣ ብር/ በመክፈል ከሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ዘወትር ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ከዋናው መ/ቤት /አዲስአበባ/ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሠዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት ሠነዶች በጥቅል 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ አካቶ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጧቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታው ያሸነፉትን ሠነዶች ሙሉ ክፍያ በ 10 /አሥር/ የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሳ ከ15ኛው ቀን በኋላ ላላነሳበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ቅጣት የሚከፍል ይሆናል፡፡
- ቦክስ ፋይሉን እና ወቀቱን የመለያ፣ የማስመዘኛ፣ የማጓጓዣና ተያያዥ ክፍያዎች በአሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሠነዶቹን ማስጥራዊነት በመጠበቅ ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-4-16-73-47/ 011-4-66-93-36 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያንግድሥራዎችኮርፖሬሽን
የግዥ፣ ንብረትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ቡድን አስተባባሪ
አድራሻ፡- በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት
ስልክቁጥር 0114-16-73-47/011 466-93-36 አዲስአበባ-ኢትዮጵያ