የንኮማድ ኮንስትራክሽ ኃ.የ.የግ.ማ ያሉትን ቋሚ ንብረቶች ለ International Financial Reporting Standards (IFRS) ግብአት ዋጋ ትመና (Valuation) ማሰራት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

Yencomand-Construction-Logo

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 06/19/2022
 • Phone Number : 0115533766
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/25/2022

Description

የቋሚ ንብረት ዋጋ ትመና valuation of fixed assets የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን የንኮማድ ኮንስትራክሽ ኃ.የ.የግ.ማ ያሉትን ቋሚ ንብረቶች ለ International Financial Reporting Standards (IFRS) ግብአት ዋጋ ትመና (Valuation) ማሰራት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

 • IFRS በሚጠይቀው መሰረት የዋጋ ትመናውን ስራ የሚሰራ፡፡
 • የቋሚ ንብረት ዋጋ ትመናውን በከፍተኛ የሞያ ስነምግባር የሚሰራ፡፡
 • 5 ዓመትና ከዚያ በላይ በዚህ ስራ ላይ የቆየ እንዲሁም የሰራቸውን ስራዎች አስተያየት (Recommendation) ማቅረብ የሚችልና 2 እና ከዚያ በላይ የኮንስታራክሽን ድርጅት የሰራ፡፡
 • በአጭር ጊዜ ውስጥ በሚፈለገው ጥራት መስራት የሚችል፡፡
 • በህግ በተፈቀደለት አካል የተሰጠ የሙያ ፍቃድ (Certificate Of Professional Competence) ያለው ፡፡
 • የታደሰ የ 2014 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
 • የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት (TIN certificate) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት (ተመዝጋቢ ከሆነ) ማቅረብ የሚችል፡፡
 • ከላይ የተገለፁትን የምታሟሉ በድርጅቱ ቢሮ በመገኘት የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላል፡፡ ከሰኔ 13/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 17/2014 ዓ.ም፡፡
 • የቴክኒካል እና ፋይናሽያል ፕሮፖዛል በተለያየ ፖስታ ከ 10,000.00 ብር የጨረታ ማስከበሪያ CPO ወይም unconditional bank guarantee ጋር ከቀን ሰኔ 18/2014 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በፊት ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 • ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 18/2014 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ይከፈታል፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ቦታው ደምበል ሲቲ ሴንተር ቅጥር ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር፡- 03 ስልክ ቁ.0115533766

ማሳሰቢያ፡-

 • ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰውን ቁጥር በመደወል ወይም በአካል በመገኘት ከጨረታው ጋር የተያያዘ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 • የንኮማድ ኮንስትራክሽ ኃ.የ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡