ቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር የአዋጭነት ጥናት (Feasibility Study) በዘርፉ ብቁ በሆነ የማኔጅመንት አማካሪ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Engineering Related Consultancy
  • Posted Date : 06/22/2022
  • Phone Number : 0111332824
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/28/2022

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመርካቶ አካባቢ በተለምዶ አሜሪካ ግቢ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ እያስገነባ በሚገኘው ባለ14 ፎቅ ቅይጥ አገልግሎት ሕንጻ ግንባታ እያስገነባ ይገኛል፡፡

የሕንጻው ግንባታ የሚገኝበት ደረጃም ከመሬት በላይ ሁለተኛ ወለል አርማታ ሙሌት ላይ ሲሆን የፕሮጀክን የአዋጭነት ጥናት (Feasibility Study) በዘርፉ ብቁ በሆነ የማኔጅመንት አማካሪ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳረፍ የምትፈልጉ አማካሪ ድርጅቶች

  1. የ2014 በጀት ዓመት ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ፣ የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ቲን( Tin) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ እና ግብር የከፈሉበት ታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የጥናት ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አጠናቅቀው ማስረከብ የሚችሉ

መሆን የሚጠበቅባቸው ሲሆን ተጫራጮች የድርጅታቸውን ብቃት የሚያረጋግጥ ድርጅታዊ ዝርዝር መግለጫ (Company Profile) ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት የሥራ ቀናት ኃብተጊዮርጊስ ድልድይ ኩርቱ ሕንጻ 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የድርጅታችን ቢሮ በመምጣት ማስረከብ የምትችሉ መሆኑን እናሳሳቃል፡፡

ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቅጥር +251 111 33 28 24 ደውለው ይጠይቁን፡፡