ያሜት ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ በመገናኛ አካባቢ ለሚገነባው ያዶት ታወር 3B+G+M+23 ህንጻ ግንባታ የማጠናቀቂያ ስራዎችን ህጋዊ የስራ ፍቃድ ያላቸውን ሰብ ኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።

yamet-construction-plc-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 07/02/2022
 • Phone Number : 0116929292
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/08/2022

Description

 በድጋሚ  የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ያሜት ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ በመገናኛ አካባቢ ለሚገነባው ያዶት ታወር 3B+G+M+23 ህንጻ ግንባታ የማጠናቀቂያ ስራዎችን ህጋዊ የስራ ፍቃድ ያላቸውን ሰብ ኮንትራት ለማሰራት ስለፈለገ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን ዝርዝር መረጃዎች ማሟላት ይጠበቅባችዋል፡-

 1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፍኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
 2. በዘርፉ ብቁ የስራ ልምድ ያላቸው፣ የግድግዳ (HCB)፤ የልስን (Plastering) የወለል (Screed) ስራ፤ የብረት (Reinforcement Bar)፤ የፎርምወርክ (Formwork)  እና የፊኒሺንግ (የግድግዳ፤ የሲሊንግ ስራ)  ላይ በጥራት እና በብቃት ትልልቅ ህንጻዎች ላይ የሰሩ እና ማስረጃ (ስራው ያለቀ ከሆነ የስራ አፈጻጸም ደብዳቤ፣ ስራው በሂደት ላይ ካለ የስራው ውል ወይም የክፍያ ሰርተፊኬት) ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
 3. ተጫራቾቹ የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 ብር በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል።
 4. ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፤30 ሰዓት እስከ ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ መገናኛ ስለሺ ስህን ህንጻ 11ኛ  ፎቅ ያሜት ኮንስትራክሽን ቢሮ ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላሉ።
 5. ተጫራቾቹ ቴክኒካል ዶክመንት እና ፋይናንሺያል ዶክመንቶቹን በተለያየ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 5ኛው ቀን 9፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ።
 6. ጨረታው በ5ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቢሮ የጨረታ ኮሚቴ በተገኙበት ቴክኒካል ዶክመንቶች ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል።
 7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 8. የሚፈለጉት የስራዎችን እና ዓይነትና ብዛት ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን።
 9. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-116-92-92-92/93/94/95 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ ።

ያሜት ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ