የሲሚንቶ ማሸጊያ ከረጢቶችን ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው የሀገር ውስጥ አምራቾችና አቅራቢዎች ላይ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Habesha-Cement-logo-1

Overview

  • Category : Purchases
  • Posted Date : 07/02/2022
  • Phone Number : 0114163273
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 07/12/2022

Description

 ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ

 የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

Purchase bid No.01/PP Bag/2022

ኩባንያችን የሲሚንቶ ማሸጊያ ከረጢቶችን ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው የሀገር ውስጥ አምራቾችና አቅራቢዎች ላይ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ማንኛውም ተጫራች ስለጨረታው እና የከረጢቱን ዓይነት እንዲሁም ተያያዥ መመሪያዎችን የያዘውን የጨረታ ሠነድ ከኩባንያችን ዋናው መስሪያ ቤት ካዛንቺስ ኢሊሌ ሆቴል አዲሱ ህንፃ ከሚገኘው ህንጻ 19ኛ ፎቅ ሶርሲንግ እና ግዢ መምሪያ በመቅረብ በሚሰጡት የኢሜይል አድራሻ ሰነዱን በመውስድ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ፡- ብር 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር ብቻ): በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራች ድርጅቶች የምታቀርቡትን የከረጢት ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መሰረት በማቅረብ ሆለታ ፋብሪካችን ድረስ የምታቀርቡበትን የነጠላ ዋጋ እና ተያያዥ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ እስከ ሐምሌ 05 ቀን 2014 ዓ.ም ከላይ በተመለከተው የኩባንያችን ዋና መ/ቤት አድራሻ እንድታስገቡ እንጠይቃለን፡-

ጨረታው ሐምሌ  05 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 5፡30 ከላይ በተገለጸው አድራሻ በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሐበሻ ሲሚንቶ አ.

ስልክ ቁጥር 011-4163273