የከሰረው ጥምረት አግሮ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር አካል የሆነው የከሰረው በረኸ ማውንቴን ኃ/የተ/የግል ማሕበር ንብረት የሆነውን የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ከእነሙሉ ድርጅቱ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : House & Building Sale
 • Posted Date : 07/06/2022
 • Phone Number : 0913580342
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/30/2022

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የከሰረው ጥምረት አግሮ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር አካል የሆነው የከሰረው በረኸ ማውንቴን ኃ/የተ/የግል ማሕበር ንብረት የሆነውን የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ከእነሙሉ ድርጅቱ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የጨረታው መነሻ ብር 18,616,000.00 (አስራ ስምንት ሚሊዮን ስድስት መቶ አስራ ስድስት ሽህ ብር) ነው፡፡ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ግለሰቦች ተቋማትና ድርጅቶች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሰንዳፋ ከሚገኝው የድርጅቱ ጽ/ቤት ወይም አዲስ አበባ ከኪሳራ አጣሪዎች በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይቻላል፡፡

ለጨረታ የቀረቡ የድርጅቱ ንብረቶች በ2.1 ሄክታር (21,000 ካሬ ሜትር) የመሬት ስፋት ባለው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ ላይ ያረፈ/የሚገኙ የወተት ማቀነባበሪያ መሳሪያዎች፤ የተለያዩ ቤቶች እና የማዕድን ውሃ ለማምረት የሚያስችል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ወዘተ… ናቸው፡፡

ንብረቶቹ የሚገኙት የከሰረው በረኸ ማውንቴን አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር በሚገኝበት ሰንዳፋ ከተማ ቀበሌ 01 ከፖሊስ ዩኒቨርስቲ በስተጀርባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ወተት ማቀነባበሪያ ጣቢያ ውስጥ ነው፡፡

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፤

 1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1% ብር 186,160.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ንብረቶቹን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ በሚገኝበት ሰንዳፋ ከተማ ቀበሌ 01 ከፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በስተጀርባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ ውስጥ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ፤ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት ድርጅቱ ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሐምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋት 4፡00 ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ለይ ይከፈታል፡፡
 4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ በ20 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ገንዘቡ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ካልተከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
 5. ከስም ዝውውር ጋር የተገናኙ ወጪዎችን ገዥው ይከፍላል፡፡ ንብረቶቹ የሚፈለግባቸው ማናቸውም ውዝፍ እዳ ቢኖር ሻጭ ይሸፍናል፡፡
 6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913580342 ወይም 0911969426 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የከሰረው በረኸ ማውንቴን አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር