ዳሸን ባንክ አ.ማ. ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

Dashen-Bank-Logo-Reportertenders-2

Overview

  • Category : Industry & Factory Foreclosure
  • Posted Date : 07/06/2022
  • Phone Number : 0115180351
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 08/09/2022

Description

ዳሸን ባንክ አ.ማ.
የጨረታ ማስታወቂያ

ተ.ቁ የተበዳሪው  ስም  

አበዳሪው ቅርንጫፍ

የአስያዥ ስም ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የንብረቱ ዓይነት የጨረታው መነሻ ዋጋ ጨረታው  የሚካሄድበት
ከተማ ወረዳ ቀበሌ የካርታ ቁጥር የቦታ ስፋት ቀን ሰዓት ቦታ
1    11. አቶ አብዱረዛቅ ወርቅቾ ዲላ ተበዳሪው ጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ አዳሜ መያድ

00172

2.38 ሄክታር የውሃ ማሸጊያ ፋብሪካ 20,294,498.00 ነሐሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. 4፡00 ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ

1. ተጫራቾች ብሔራዊ ባንክ አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት 6ኛ ወለል ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ ፣ ዲላ እና አዋሳ ዲስትሪክት የባንኩ ቀጠና ጽ/ቤት በአካል ቀርበው የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ ፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% የጨረታ ማስከበርያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለጨረታ ወስደው ከሞሉት ሠነድ ጋር ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚመቻቸው ቦታ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያላካተተ(ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት) መሆን አለበት፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበውን ንብረት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 ከሰዓት 7፡00 – 11፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ቦታው ላይ በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡ ይርጋጨፌ ቅርንጫፍ ስልክ ቁጥር 046-332-11-58 ፣ 046-332-12-46
3. ጨረታው በሠንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በዋናው መሥሪያ ቤት ፣በአዋሳ ቅ/ጽ/ቤት፣በዲላ ቅርንጫፍ የኮሚቴ አባላት ባሉበት ይከፈታል ፡፡
4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ባይከፍል ግን ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ከጨረታው እንዲወጣ ይደረጋል ፡፡
5. የጨረታ አሸናፊው በሚገዛው ንብረት ላይ የሚፈለግ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ግብር፣ታክስ፣የስም ማዛወርያ እና የሊዝ ክፍያዎች ይመለከታቸዋል፡፡
6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው
• ለተጨማሪ መረጃ ዲላ 046-3-31-09-82 046-331-36-05፣ አዋሳ 046-212-54-16 / 046-212-65-36/ 046-212-65-33 ዳሸን ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 011 –5- 18 – 09- 13 ፣ 011-5-18-03-51 የውስጥ መስመር 0115 3143 ፣ 3144 በመደወል መጠየቅ ይቻላል ፡፡