ቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር የ2014ዓ.ም ብዛቱ 5 ቦክስ ፋይል የሂሳብ እንቅስቃሴ በተፈቀደለት የውጪ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Auditing Related
  • Posted Date : 07/11/2022
  • Phone Number : 0118332824
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 07/22/2022

Description

የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

 ማህበራችን ቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር የ2014ዓ.ም ብዛቱ 5 ቦክስ ፋይል የሂሳብ እንቅስቃሴ በተፈቀደለት የውጪ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1ኛ. በሙያው የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ

2ኛ. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር ያለው

3ኛ. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

ተጫራቾች ይህ ማስተወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የኦዲት አገልግሎት ስራውን የምታከናውኑበትን ዋጋና፣ ሥራውን አጠናቆ የኦዲት ሪፖርቱን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ጊዜ በፅሁፍ ገልፃችሁ የጨረታ ሰነዳችሁን በሰም በታሸጋ ኤንቨሎፕ በማህበሩ ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

የማህበሩ አድራሻ፡- ኩርቱ ህንፃ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ ከተፈራ ህንፃ ጎን የቢሮ ቁጥር 803 

ለበለጠ መረጃ፡- የስልክ ቁጥር 0118-332824/0900-333414