ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ኃ/የተ/የግል ማህበር ሲሚንቶ ለማምረት የሚጠቀምበትን ጥሬ ዕቃ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

Derba-Midroc-cement-plc-logo

Overview

  • Category : Vehicle Purchase
  • Posted Date : 07/11/2022
  • Phone Number : 0944745113
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 07/15/2022

Description

በድጋሜ የወጣ የመኪና ኪራይ ጨረታ

ድርጅታችን ሲሚንቶ ለማምረት የሚጠቀምበትን ጥሬ ዕቃ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ታትት ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሠዓት  ጊዮን ሆቴል አጠገብ ከሚገኘው ናኒ ህነፃ 12ኛ ፎቅ የግዥና አቅርቦት ምመሪያ ቢሮ  የታደሰ የንግድ ፈቃድ አሪጂናልና ኮፒ በመያዝ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋና የጨረታ ዝርዝር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲሁም ብር ሁለት መቶ ሺህ የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/  CPO ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በማያያዝ በተመሳሳይ የቢሮ አድራሻ ከጨረታ መዝጊያ ሠዓት በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው የሚዘጋበት ዕለት ሓምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም.  ከቀኑ 10፡30 ሲሆን ጨረታው ሓምሌ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ አሸናፊ ድርጅት የኪራይ ውሉን ከመፈራረሙ በፊት ብር አንድ ሚሊዮን በ CPO ወይም ቅድመ ሁኔታ በሌለው የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡

ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ኃ/የተ/የግል ማህበር

የግዥና አቅርቦት መምሪየ ቢሮ

ናኒ ህንፃ 12ኛ ፎቅ፣ ስ.ቁ 0944745113/0115549875

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ