ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር በፉሪ ባቡር ጣቢያ ላለው የኮንክሪት ባቺንግ ፕላንት ስራ የሚውል የአርማታ ጠጠር እና አሸዋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Tracon-Trading-Logo

Overview

 • Category : Construction Raw Materials
 • Posted Date : 07/11/2022
 • Phone Number : 0989098625
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/15/2022

Description

 የጨረታ ማስታወቂያ

ጠጠር እና የወንዝ አሸዋ  ጨረታ ቁጥር፡33/2022/10

ኩባንያችን ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር በፉሪ ባቡር ጣቢያ ላለው የኮንክሪት ባቺንግ ፕላንት ስራ የሚውል የአርማታ ጠጠር እና አሸዋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የ01 እና የ02 ጠጠር፤ የወንዝ አሸዋ የማቅረብ ልምዱ እና ብቃቱ ያላቸውን አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

ተወዳዳሪዎች ለቴክኒካል ምዘና ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ተዛማጅ ስራወች አፈጻፀም የሚያሳይ ዶክመንቶች እንዲያቀርቡ ሲጠበቅ፤ለፋይናንሻል  ምዘና የሚያቀርቡትን የጠጠርና አሸዋ ናሙና በማዳበሪያ በማቅረብ፤ላቀረቡት ናሙና ነጠላ ዋጋ/ከቫት በፊት/ በታሸገ ፖስታ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተ/ቁ የስራው/አቅርቦት ዝርዝር መለኪያ የፍላጎት መጠን ልዩ መግለጫ
1 ለፓምፕ ኮንክሪት ሊሆን የሚችል ጥራትና ስፔስፊኬሽን ያሟላ 02 ጠጠር/19ሚ.ሜ ሳይዝ ሜ/ኪዩብ 10000 ስታንዳርዱን የጠበቀ ምርት
2 ጥራትና ስፔስፊኬሽን ያሟላ 01 ጠጠር ሜ/ኪዩብ 10000 ስታንዳርዱን የጠበቀ ምርት
3 ጥራትና ስፔስፊኬሽን ያሟላ የወንዝ አሸዋ ባቺንግ ፕላንት ድረስ ማቅረብ ሜ/ኪዩብ 10000 ስታንዳርዱን የጠበቀ ምርት

መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

 1. ተጫራቾች የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፍቃድ እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
 2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100 ብር/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከትራኮን ሪል ስቴት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
 3. የጨረታ ዋስትና ብር ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2 ፕርሰንት በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 4. የጨረታ አሸናፊው በአንድ ሳምንት ውስጥ ውሉን ጨርሶ እቃውን ማቅረብ አለበት፡፡
 5. ተጫራቾች እቃውን በአካል ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
 6.  ነጠላ ዋጋ ለሞላባቸው የአቅርቦት ማቴሪያሎች  በቂ ናሙና ማስገባት ይኖርበታል፡፡የትራንስፖርት ዋጋ ለብቻው በማስታወሻ መገለጽ አለበት ከነጠላ ዋጋው ጋር መደመር የለበትም፡፡
 7. ይህ ጨረታ በመጀመሪያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቡኃላ ባሉት 6 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፤ሀምሌ 8/2014 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

– ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም

 ለበለጠ መረጃ

ጀሞ 1-ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ

ስ.ቁ 0989098625/0913098889