ዘመን ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር አክሲዮኖችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

Zemen-Insurance-Share-Company-logo

Overview

  • Category : Share Foreclosure
  • Posted Date : 10/03/2022
  • Phone Number : 0116151125
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/14/2022

Description

አክሲዮኖችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

ዘመን ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ለማህበሩ ባለአክሲዮኖች ተደልድለው ተራፊ የሆኑትን በቁጥር 299 የሆኑ    አክሲዮኖችን የአንዱ አክሲዮን ዋጋ ብር 5000.00 ሆኖ ጠቅላላ ዋጋቸው ብር 1,495,000.00 (አንድ ሚሊየን አራት መቶ ዘጠና አምስት ሺ) የሚያወጡ አክሲዮኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች የተዘጋጀውን ዝርዝር መመሪያ ቦሌ መንገድ ከሚገኘው ዓለም ህንጻ 2ኛ ፎቅ የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ ከመስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የአክሲዮን መጠን በተዘጋጀው ቅፅ ላይ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ   ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 4  ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ጥቅምት 4 ቀን 2015ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማህበሩ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-116-15-11-25 መደወል ይችላል፡፡