ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በዋስትና የያዘውን ንብረት ባሉበት በሐራጅ ይሸጣል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 02/06/2023
- Closing Date : 03/07/2023
- Phone Number : 0115572107
- Source : Reporter
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በዋስትና የያዘውን ንብረት ባሉበት በሐራጅ ይሸጣል፡፡
ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | ለጨረታ የቀረበው መያዣ ንብረት | አበዳሪው ቅርንጫፍ | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት | የጨረታ መነሻ/ዋጋ በብር | የጨረታዉ ቀንና ሰዓት | ጨረታው የወጣው | ||||
ከተማ | ቀበሌ/ወረዳ | የካርታ ቁጥር | የቦታ ስፋት በካ.ሜ | ቀን | ሰዓት | |||||||
1. | አቶ ሲሳይ ጫላ | ወ/ሮ ሰላማዊት ፍሰሃ | መኖሪያ ቤት | ጉለሌ | ቡራዩ | ቡራዩ ከታ | BUR/1999/98 | 200 | 2,762,466.30 | 29/06/2015 | 3፡00-5፡00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
2. | አቶ መለሰ መገርሳ | ወ/ሮ ሾላዬ አስቻለው | መኖሪያ ቤት | አሳሳ | ሻሸመኔ | አሌሉ | 17858 | 280 | 1,636,935.01 | 30/06/2015 | 4፡00-6፡00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
- ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ አሰርተው ከጨረታው ቀን በፊት ማስያዝ ወይም ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ተ.ቁ 1 በኦሮሚያ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 12ኛ ፎቅ፣ ተ.ቁ 2 በኦሮሚያ ባንክ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
- በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው የጨረታ ቀን ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ጨረታውን ካካሄደው የባንኩ ክፍል ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብም አይመለስለትም፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ብድርን በተመለከተ ቀርቦ የባንኩን የብድር መምሪያ ማነጋገር ይችላል፡፡
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 2107/011 558 6497 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ወይም ለተ.ቁ 1 በ011 273 2015/07 ጉለሌ ቅርንጫፍ፤ ለተ.ቁ 2 በ022-336 0073/03 አሳሳ ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ጨረታው ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም ብድሩ ከተከፈለ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ለመንግስት የሚከፈለውን የስም ማዛወሪያ፤ አስፈላጊ ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡
- የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ የሚከፈለውን ክፍያ ለመክፈል ንብረቱ በሚገኝበት የወረዳ ወይም ከተማ አስተዳደር በመቅረብ የሊዝ ውል መዋዋል አለበት፡፡
ኦሮሚያ ባንክ