የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ አላቂ፣ ቋሚ ዕቃዎችና አገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Athletics-Federation-የኢትዮጵያ-አትሌቲክስ-ፌዴሬሽን-Logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 01/16/2021
 • Phone Number : 0116479794
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/26/2021

Description

ጥር 06/2013 ዓ.ም

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን አላቂ፣ ቋሚ ዕቃዎችና አገልግሎት ግዥዎችን በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 • አላቂና የጽዳት ዕቃዎች፤
 • የኤሌክትሮኒክስና የጥገና መሣሪያዎች፣
 • የስፖርት መሣሪያዎች፤
 • ኮምፒውተርና ተዛማች ዕቃዎች፤
 • የመኪና ጎማዎች፣ ቅባቶችና ዘይቶች፤
 • የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር ዕቃዎች፤
 • የጽሕፈት መሣሪያዎች፤
 • የደንብ ልብስ፤

በዚሁ መሠረት፡-

 1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግስት ግ/ን/አስ/ ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገበ፤ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነድ ጋር የሚያቀርቡትን ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 5% አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 00(ሃምሳ ብር) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በድርጅቱ 2ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 2 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ  ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል፡፡  
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሣጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ዕቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

       አድራሻ፡-  ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ፡- 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፋክስ 0116-45-08-79

ፖ.ሳ.ቁ 13336

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

 

Send me an email when this category has been updated