የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለዋናው መ/ቤት አገልግሎት የሚውል በኢንፎርማሽን ኮምንኬሽን ቴክኖሎጂ ዝርጋታ “Enterprise resource planning” /ERP/ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Defence-Construction-Enterprise-5

Overview

  • Category : Computer Accessories
  • Posted Date : 04/05/2021
  • Closing Date : 04/23/2021
  • Phone Number : 0118867031
  • Source : Reporter

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCDE 004/2013

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለዋናው መ/ቤት አገልግሎት የሚውል በኢንፎርማሽን ኮምንኬሽን ቴክኖሎጂ ዝርጋታ “Enterprise resource planning” /ERP/ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም:-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ “Tin” ሰርተፊኬት እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው የታክስ ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለሌሎች ተቋማት “Enterprise resource planning” (ERP) የሰሩበት በደብዳቤ የተረጋገጠ የልምድ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO፣በባንክ ጋራንቲ ወይም በቼክ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የድርጅቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ቴክኒካል ፕሮፓዛሉ ብቻ ተከፍቶ ፋይናንሻል ፕሮፓዛሉ ደግሞ ቴክኒካል ግምገማው ካለቀ በኃላ በግምገማው ላለፉ ድርጅቶች ብቻ ፋይናንሻል ፕሮፓዛሉ ሲከፈት እንደገና በደብዳቤ የሚገለጽላቸው ይሆናል፡፡
  5. ድርጅታችን ከዚህ በላይ ባወጣው የጨረታ ማስታወቂያ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ቀናት ውስጥ በስራ ቀን ድርጅቱ በሚገኝበት አድራሻ ወሎ ሰፈር አካባቢ አምባሰል ህንፃ ፊት ለፊት ወይም ብራና ማተሚያ ድርጅት ዝቅ ብሎ በድርጅታችን ዋናው መ/ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከግዥ ክፍል የጨረታ ሰነዱን ሀርድ ኮፒና ሶፍት ኮፒ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  6. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 አድራሻ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

የቀጥታ ስልክ ቁጥር   0118960632, 0118867031