ድርጅታችን ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ወልመል መስኖ ፕሮጀክትና ባሌ ሮቤ ከተማ ደረስ በጠቅላላው 25,445 ኩንታል ሲሚንቶ ማጓጓዝ ይፈልጋል

Alemayehu-Ketema-General-Contracter-logo-reportertenders

Overview

  • Category : Transport Service
  • Posted Date : 04/21/2021
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 04/26/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር AKGC 001/13

  ድርጅታችን ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ወልመል መስኖ ፕሮጀክትና ባሌ ሮቤ ከተማ ደረስ በጠቅላላው 25,445 ኩንታል ሲሚንቶ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ከባሌ ሮቤ ከተማ በኋላ ከነተሳቢ ለማጓጓዝ ስለማይቻል፣

– ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ እስከ ወልመል መስኖ ፕሮጀክት ድረስ 200 ኩንታል የመያዝ አቅም ያለው የጭነት ተሽከርካሪ፣

-ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ እስከ ባሌ ሮቤ ከተማ ድረስ 400 ኩንታል መያዝ አቅም ያለው የጭነት ተሳቢ ተሽከርካሪ ማቅረብ የሚችሉ የትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችን ይጋብዛል፡፡

1ኛ.ተጫራቾች ለ2013 ዓ.ም የሥራ ዘመን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተ.እ.ታ እና የግብር ከፋዮች የምዝገባ ሰረተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2ኛ. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች የስራ አፈጻጸም ዋስትና ብር 50,000 ማስያዝ አለባቸው፤

3ኛ.  በትራንስፖርት የሥራ ዘርፍ ላሠማራቸው ተሽከርካሪዎች በመቆጣጠር፣በማሠማራትና ሥራ በመምራት በቂ የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችል፣

4ኛ.   ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ እስከ ሚያዚያ 18 ቀን 2013ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሠዓት ድረስ ከጃክሮስ ወደ የረር በሚወስደው መንገድ ሌቃ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 405 ማቅረብ ይኖርባቸዋል:

 ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡