ዳሸን ባንክ ለንግድ ሥራ ለሚጓዙ ደንበኞቹ የዴቢት ካርድ ይፋ አደረገ | Ethiopian Reporter Tenders | 2merkato | ጨረታ

ዳሸን ባንክ ለንግድ ሥራ ለሚጓዙ ደንበኞቹ የዴቢት ካርድ ይፋ አደረገ

ዳሸን ባንክ ከኢትዮጵያ ውጭ ለንግድ ሥራ የሚጓዙ ደንበኞቹ ግብይታቸውን በውጭ ምንዛሪ ለመፈጸም የሚያስችላቸው የዴቢት ካርድ ይፋ ሲያደርግ፣ አቢሲኒያ ባንክ ደግሞ ዓይነ ሥውራን የሚገለገሉበት ኤቲኤም አገልግሎት ላይ አዋለ፡፡ ሁለቱ ባንኮች ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ያደረጉዋቸው አዲሶቹ አገልግሎቶቻቸው በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የሚተገበሩ ስለመሆናቸው ባንኮቹ በሰጡዋቸው መግለጫዎች አመልክተዋል፡፡ ዳሸን ባንክ አሜሪካን ኤክስፕሬስ የተሰኘውን …

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደረቅ ጭነት ላይ ዋጋ ጨመረ | Ethiopian Reporter Tenders | 2merkato | ጨረታ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደረቅ ጭነት ላይ ዋጋ ጨመረ

በነዳጅ ምርት ላይ የሚጣለው ታክስ እየጨመረ በመምጣቱ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደረቅ ጭነት የአገልግሎት ዋጋ ላይ የተወሰነ ጭማሪ ማድረጉንና በሌሎች አገልግሎቶቹም ላይ ተመሳሳይ ጭማሪ እንዳደረገ አስታወቀ፡፡ ይህንን አዲሱን ታሪፍም ከሰኞ ጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚተገበር በተለይ ለደረቅ ጭነት አገልግሎት ተጠቃሚዎቹ በላከው መልዕክት አስታውቋል፡፡ አየር መንገዱ በጭነት አገልግሎቱ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉን ለአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንበኞቹ …

ዳሸን ባንክ ዳያስፖራው የውጭ ገንዘብ የሚልክበትን ሥርዓት ዘረጋ | Ethiopian Reporter Tenders | 2merkato | ጨረታ

ዳሸን ባንክ ዳያስፖራው የውጭ ገንዘብ የሚልክበትን ሥርዓት ዘረጋ

በሕጋዊ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚላከው የውጭ ምንዛሪ ሬሚታንስ በዓመት ወደ አምስት ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ይገመታል፡፡ ከዳያስፖራው ወደ አገር ቤት በሕጋዊ መንገድ ከሚላከው ምንዛሪ ይልቅ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የሚላከው የገንዘብ መጠን ብልጫ አለው ተብሎም ይታመናል፡፡ ወደ አገር ውስጥ የሚላከው ገንዘብ ሕጋዊ መስመርን ተከትሎ በባንክ በኩል ላለመላኩ አንዱ ምክንያት፣ በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል ሲላክ የሚጠየቀው …

የውጭ ምንዛሪን በገበያ ዋጋ የተመሠረተ የማድረግ ሒደት | Ethiopian Reporter Tenders | 2merkato | ጨረታ

የውጭ ምንዛሪን በገበያ ዋጋ የተመሠረተ የማድረግ ሒደት

የውጭ ምንዛሪ እጥረትና ከዚሁ ጋር ተያይዘው ያሉ ለዘመናት ያልተፈቱ ችግሮች ዛሬም በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ኢኮኖሚያዊ ስንክሳሮች መካከል  ይጠቀሳሉ፡፡ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ብቻ ሳይሆን የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ከማስተዳደር አንፃር ያለው ክፍተትም የችግሩ አካል ነው፡፡ ጥቁር ገበያ ጎልቶ መውጣትና ከመደበኛው የምንዛሪ ዋጋ አሻቅቦ መገኘቱ እንዲሁም የጥቁር ገበያው ጉልበት መታየት ሁኔታውን አብሶታል፡፡ ያለውን እጥረት ተከትሎ የሚታየው ሕገወጥ ሥራም …

መርካቶዎች እየተፈተኑባቸው ያሉ ችግሮች | Ethiopian Reporter Tenders | 2merkato | ጨረታ

መርካቶዎች እየተፈተኑባቸው ያሉ ችግሮች

ከሁለት አሠርት በላይ በንግድ ላይ ለተሰማራው አቶ ቴድሮስ ፍቅሩ፣ መርካቶ ማለት ከሰፈርም ከመነገጃነትም በላይ ነው። ‹‹ተወልጄ አድጌ ሀብት ያፈራሁባት ልዩ ሥፍራ ናት›› በማለት መርካቶን ያወድሳል የ43 ዓመቱ ጎልማሳ አቶ ቴድሮስ። በልብስ ምርቶች ንግድ፣ በቤትና ቢሮ ዕቃዎች ማምረትና መሸጥ ላይ የተሰማራው አቶ ቴድሮስ፣ በመርካቶ ሕይወቱን ከልጅነት እስከ አዋቂነት ቢያሳልፍም በመዲናዋ ነግዶ ሀብት ማፍራት ቀላል እንዳልሆነ ያነሳል። ‹‹ምንም እንኳን መርካቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ምርት የሚከፋፈልባትና የሚቀርብባት የሁላችንም የገበያ መዲና ብትሆንም፣ ከቀን ወደ ቀን ሠርቶ መለወጥ እየከበደ ነው›› የሚለው አቶ ቴድሮስ፣ ለዚህም መንግሥትና ሕገወጥ ነጋዴዎችን ይወቅሳል። ከ30 ሺሕ በላይ ሱቆችና ከ700 ሺሕ በላይ ሸማቾች፣ ነጋዴዎችና የንግድ ሠራተኞች በየቀኑ ገብተው ይወጡባታል ተብሎ በምትታመነው መርካቶ፣ የተለያዩ ችግሮችን መመልከት አዲስ ነገር አይደለም። ከሌባና ቀማኞች ገንዘብና ንብረታቸውን ለመጠበቅ ከሚሞክሩ ሸማቾች እስከ በሙስና የተዘፈቁ አንዳንድ የገቢዎች ሠራተኞች ለመሰወር የሚሞክሩ ሠራተኞችን ማየት የተለመደ ጉዳይ ነው። ሁሉም ዓይነት ነጋዴዎች በየፊናቸው እንደ ዘርፋቸው ሁኔታ የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢገጥማቸውም ሪፖርተር በመርካቶ በመገኘት ባደረገው ዳሰሳ በአብዛኛው የሚያነሱት ቅሬታዎች ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓት አለመኖር፣ ለሙስና በር የከፈተ የተጨማሪ እሴት ታክስ አተገባበርንና የመሠረተ ልማቶች አለሟሟላትን ነው። ‹‹የፍትሐዊንግድያለ›› የፌዴራልም ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የወረዳ ንግድ ቢሮዎች የተገልጋዮች ቻርተር ላይ በጉልህ ከተቀመጡ ጉዳዮች አንዱ ፍትሐዊ፣ ግልፅና በውድድር ላይ የተመሠረተ የንግድ ሥርዓትን ማስፈን ነው። ይህንንም መተግበር ከመንግሥት አጀንዳዎች መካከል መሆኑን የመንግሥት ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ያነሳሉ። ይሁን እንጂ የተጻፈው አልያም የተወራው ከትግበራው አኳያ ፈፅሞ የተለየ መሆኑን ነጋዴዎች ይናገራሉ። በመርካቶ አመዴ ተራ በጫማ ችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩት አቶ አማኑኤል መንግሥቱ እንደሚናገሩት፣ የንግድ ሥርዓቱ ላይ የፍትሐዊነት ችግሮች መታየት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። የመንገድ ላይ ንግድ መስፋፋትን እንደ ማሳያ የሚያነሱት አቶ …

ለስምንት ዓመታት በኪራይ መጋዘን የተቀመጡ 485 ሺሕ ኩንታል የማዳበሪያ ግብዓቶች ለጨረታ ቀረቡ | Ethiopian Reporter Tenders | 2merkato | ጨረታ

ለስምንት ዓመታት በኪራይ መጋዘን የተቀመጡ 485 ሺሕ ኩንታል የማዳበሪያ ግብዓቶች ለጨረታ ቀረቡ

ከስምንት ዓመታት በፊት በግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽንና በክልል ማኅበራት በ657 ሚሊዮን ብር የተገዛው 485 ሺሕ የማዳበሪያ ግብዓት፣ ለበርካታ ዓመታት በኪራይ መጋዘን ያለ ምንም ጥቅም ከተቀመጡበት ወጥተው ለጨረታ መቅረባቸው ተነገረ፡፡ በግብርና ሚኒስቴር ትዕዛዝ በ2006 ዓ.ም. የተገዛው ፖታሽ፣ ዚንክና ቦሮን የተሰኙ የማዳበሪያ ግብዓቶች ወደ አገር ውስጥ ገብተው በቀላሉ ተቀይጠው ለአርሶ አደሩ በቅናሽ ዋጋ ለማቅረብ ታስቦ የተገዙ ቢሆንም፣ የታሰበው …

የምግብ ዘይት አቅርቦት ችግርን የመቅረፍ ተስፋ | Ethiopian Reporter Tenders | 2merkato | ጨረታ

የምግብ ዘይት አቅርቦት ችግርን የመቅረፍ ተስፋ

በአሁኑ ወቅት በገበያ ውስጥ የምግብ ዘይት እጥረት አለ፡፡ በገበያ ላይ ከተገኘም መሸጥ ከሚገባው ዋጋ በላይ እየተሸጠ ነው፡፡ በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ በሸማቾች ማኅበራት በኩል 20 ሌትር የፓልም ዘይት በ770 ብር ለሸማቾች ሲሸጥ የነበረ ቢሆንም፣ ይኼው ዘይት በነጋዴው እጅ ገብቶ መልሶ እስከ 1,600 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ በሸማቾች ማኅበራት በኩል የተከፋፈለው ይህ ዘይት በአመዛኙ ተጠቃሚዎች ለራሳቸው ፍጆታ …

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የተጋረጠበት አደጋ | Ethiopian Reporter Tenders | 2merkato | ጨረታ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የተጋረጠበት አደጋ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ችግር ውስጥ መሆኑ መነገር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው የኮንስትራክሽን ግብዓት ዕቃዎች ዋጋ ከሚገባው በላይ መሰቀል፣ የግንባታውን ዘርፍ በእጅጉ እየጎዳ ነው፡፡ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኮንትራክተሮች ማኅበር እንዳመለከተውም፣ አሁን በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ እየታየ ያለው ችግር አጠቃላይ በግንባታ ሥራዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠሩም በላይ፣ አፋጣኝ መፍትሔ ካላገኘ የበርካታ ፕሮጀክቶች ሥራ ሊቆም እንደሚችል ነው፡፡ …